Sunday, September 11, 2011

ዛቲ ጦማር

-->

ዛቲ ጦማር

ይህን ለሚያነብቡ ኹሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ሰላም ይሁን!!
እንኳን ለዐዲሱ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ (በዚህ አባባልአድራሽመኖሩን ልብ ይሏል)! ያው እንደምታስታውሱት፣ ይህ የኔና የናንተ አገር፣ለዐዲሱ ዓመት እንኳን ደረሳችሁ!” በማለት በከንቱ የሚጓደዱ ካኪ ለባሽ  ባለጊዜዎችን በየሚዲያው አስተናግዶ ያውቃል፡፡ ይህን ጕድ ዐይን ዐይታለች ጆሮም ሰምታለች፡፡ ሰውን ማዕከል ባደረገ ፍልስምና የልቦናው ትሕትና ተመጦ፣ተፈጥሮን በቊጥጥር ስር ለማድረግእንደሚቻለው በእውን ቅዠቱ የወሰነ ድኩም ፍጡርአድራሽእንደማይሻ እኒያ ወገኖች አምነው (በእነርሱ አበባልአረጋግጠው”) ነበርና! ስለዚህ፣ እንዲህ ያለው ምስኪን ፍጡር፣ በገዛ አቅሜ እና በዲያሌክቲካዊ ሒደት መርሕ ራሴው በራሴደራሽነኝ እያለ ይቃትት ዘንድ አልታከተም ነበር፡፡ ርግጥ ዛሬም የዚህ ልክፍትሰለባየኾኑ ወገኖች ከመካከላችን አልታጡም፡፡ እነሆ፣ ሁሉ ነገራቸውእኔ፣ ለእኔና በእኔእንደተለወሰ አለ፡፡ ከገጣሚ  አበባው መላኩ ስንኝ ልዋስና (እርሱ የጻፈው ስለሌላ ጕዳይ መኾኑ ሳይዘነጋ) እንዲህ ዐይነቱ ወገኔ፣ “…በከንቱ ድግግ ጠባይ የኩርማን ልቡን ወጥሮእንደተባለው የኾነበት ይመስለኛል፡፡  ለማንኛውምአድራሽአለ!
ሁሉ ከእርሱ፣ ሁሉ በእርሱ፣ ሁሉ ደግሞ ለእርሱ የኾነ ሉዓላዊአድራሽመኖሩን ማወቅ ምንኛ መታደል ነው! ለማንኛውም ለአንድ ተጨማሪ ጊዜ እንኳን አደረሳችሁ ብያለሁ!! መጪው ዘመን ለእውነት የምንኖርበት፣ ከእውነትም በሚገኘው ነፃነት ሐሴት እያደረግን የምንመላለስበት እንዲኾን ልባዊ ጸሎቴ ነው፡፡ ርግጥ ነው እንደተለመደው፣ምኞቴ ነውአላልኩም፡፡ምኞቴ ነውያላልኩት ይህ እንዲፈጸምልን ሳልመኝ ቀርቼ ሳይኾን፣ ምኞት ብቻውን ምን ይፈይዳል ብዬ ነው፡፡ የጸሎት ሰው ባልኾንም እንኳ፣ ከመመኘት ይልቅ በጥቂቱም ቢኾን  ብጸልይ ይሻላል አይደል? ጸሎትን የሚሰማ አምላክ በሰማይ አለና (መዝ ፷፭÷)፡፡ አቤት የኔ ነገር! ገና ሰላምታዬን ሳላጠናቅቅ ሁለት አንቀጽ ተገባደደ! “የቃላት ምጣኔምናምን የሚባለው ነገርድቤ በላበሉኛ! እናም በዚችው ሹልክ ብዬ ሰላምታዬን ላጠናቅቅ—“ሻሎም”!
ከሰላምታዬ በመለጠቅ ወደ ዋነኛ ሓሳቤ ባዘግምስ? ይህም ዋነኛ ሐሳብ በዚህ ጡመራ (Blogging) መጀመር ምክንያት የሚፈጠረውን የእኔንና የናንተን ትስስር ይመለከታል፡፡ ግን ይኼይመለከታልብሎ ነገር ምንድነው? ማመልከቻ የምጽፍ አስመሰልኩት አይደል? ልሰርዘው መሰል፡፡ ርግጥ መሰረዝ እችል ነበር፡፡ ነገር ግን እንዳልሰረዝኩት እንድታውቁ ስል ትቼዋለሁ፡፡ ለማንኛውም ይህን በዚህ ትቼ ወደ ፍሬ ነገሩ ልግባ፡፡ ከላይ በርእሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረውየባሰው መጣ!!...
ከዚህ በኋላስ የምር ነው፡፡ እኔ ወንድማችሁ ወይም ልጃችሁ ሰሎሞን ጡመራ ጀምሬአለሁ፡፡ ስለዚህ….ይቺ ደግሞ ልምምጥ ትመስላለች፡፡ አይ እንግዲህ! ታዲያ ምን ብዬ ልጀምር ነው? እርግጥ የሚከተለው ምርጥ ሳይኾን አይቀርም፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድና በሕይወት ብኖር፣ በሚመጡት ዘመናት ከቃለ እግዚአብሔር የተማርሁትን እና የምማረውን፣ ካደግሁበትና ከምኖርበት ማኅበረ ሰብ የቀሰምኩትንና የምቀስመውን፣ እንዲሁም፣ በትምህርት ቤትም ይሁን ከዛ ውጭ ከነበሩትና ካሉት መምህሮቼ ያካበትኩትንና ገናም በሒደት የማገኘውን እውነት አንድ ላይ በማዛነቅ በተለያዩ ርእሰ ጕዳዮች ላይ ያሉኝን ምልከታዎች ለማስነበብ እንድችል በክርስቶስ ጸጋ እጀምረው ዘንድ እነኾ መጦመሪያዬን ወጥሬአለሁ፡፡ እፎይ! ይህ ደግሞ የዐረፍተ ነገር አወቃቀርን የሚደነግጉ ሰዋስዋዊ መርሖዎችን ሳይጥስ አልቀረም መሰለኝ፡፡ በዚህ የሞኝ ጅራፍ የሚያህል ዐረፍተ ነገር ውስጥ ሰዋስዋዊ ዝንፈት ከሌለማ ጕድ ነው! “ግራም ነፈሰ ቀኝጡመራ መጀመሬን ለናንተ ለማብሠር ያደረግሁትን ሙከራ ተረድታችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እና የጡመራ ሓሳቡን እንዴት አያችሁት? አሰተያየት ብጤ ሰንዝሩ.. !
በርግጥ ይህን ነገር ስጀምረው የሚያነበኝ እንደማላጣ በቂግምትይዤ ነው፡፡ ይህም ግምቴ ከሁለት ምክንያቶች ይመዘዛል፡፡ አንደኛው፣ ከእግዚአብሔር ሉዓላዊ መግቦት አኳያ የሚታይ ነው፡፡ እርሱ፣ ቸሩ ጌታ፣ አንድም ፈጥሮኝ (መዝ. ፻፴፱÷-) ሁለትም እንደገና ፈጥሮኝ (ኤፌ ÷) ሲያበቃ፣ በእናንተ መኻከል ባዶዬን እንከወከው ዘንድ አልሰደደኝም ብዬ አምናለሁ፡፡ እርሱ ለዘሪ ዘርን ለበላተኛም መብልን ይሰጥ የለምን? “ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል” (፪ኛ ቆሮ ÷) ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ ስለኾነም፣ በዚህ የተንጣለለ የማኅበረ ሰብ ሁዳድ መኻል  (ለሌላው የሚያካፍለው ሰማያዊ ስጦታ እንደሌለው ብጤ) በከንቱ አያንከላውሰኝም ማለት ነው፡፡ እርሱ ባለጸጋ ነዋ! ይህ ዋነኛ ትምክህቴ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያቴ  አንባቢ ወዳጆቼን ይመለከታል፡፡ እናንተን ማለት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃ አለኝ፡፡ ከዚህ በፊት በተለያዩ ቦታዎች ሞነጫጭሬ የወረወርኩትን የጽሑፍጭብጦሳይንቁ ገምጠው አስተያየቶቻቸውን የሰነዘሩ ወገኖች ዙሪያዬን ከበውኛላ! አስተያየታቸው ደግሞጨምርና ጻፍየሚል ማትጊያም ነበረው፡፡ ታዲያ እንዴት አልነበብም?
የኾነ ኾኖ መወራረዳችን አይቀሬ ነው፡፡ ውርርዱም፣እኔ እኾን ከመጻፍ የምሰንፈው? ወይስ እናንተ ናችሁ ከማንበብ የምትናጠቡት?” የሚል ነው፡፡ በርግጥ አንዳች ጠቃሚ ነገር ጠብ የማይልበት፣ ቊም ነገር የማይገኝበትና እንጨት እንጨት የሚል የፊደል ግሳንግስበለጠፍኩጊዜ ሁሉ (በርግጥ የማደርገው አይመስለኝም)እያቃራችሁም ቢኾንየማንበብ ግዴታ ያለባችሁ አይመስለኝም፡፡ ታዲያ ያኔም እንኳ ያለማንበባችሁን ምክንያትበጨዋ ደንብእቅጯን ትነግሩኛላችሁ እንጂ ሹልክ ብሎ መጥፋት አይፈቀድም፡፡ እንደዛውኃ የማያነሣችኮ ነገር የገጠማችሁ እንደኾነ፣ነገርህ እንጨት እንጨት ስላለኝ ነውትላላችሁ ብዬ እጠብቃለሁ፡፡  እኔም በተቻለኝ ሁሉ ከጡመራው ገጽ እናንተን በሚመጥን ሓሳብ መጠን ተሞልቼ ላለመጥፋት እጥራለሁ፡፡
በሌላ በኵል፣ ይህ ጡመራ ሙከራ መኾኑንንም ትገነዘቡልኛላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እዚህ ሙከራ ውስጥ የገባሁትያገኘውን የወረወረ፣ ፈሪ አይባልምብዬ ነው፡፡ ወደ ሰፊው ባሕር የምወረውረውና የባሕሩን ውኃ የማምቦጫርቅበትአሳር የሚያህል ናዳባይኖረኝም እንኳን፣ በትንንሽ ጠጠሮች ጥብጠባዬ የሚፈጠሩትን የውኃ ላይ ቀለበቶች በትዕግስት እያየን እንደመም እንደኾንስ ማን ያውቃል? አንድዬ ምን ይሣነዋል? ያው ጋንስ በጠጠር ይደገፍ የለ? ለካ ዳዊትምየዘመተውበጠጠር ኖሯል! ወይ የጠጠር ነገር! ጠጣር ይሁን እንጂጠጠርዋዛ አይደለም፡፡
በተረፈ በምጫጭረው ሓሳብ ላይ ያላችሁን አስተያየት እንደምትለግሱኝ እተማመናለሁ፡፡ ብዙ ቃል ባለበት በዚያ ስሕተት አይጠፋምና፣ በጡመራው ሜዳ ልጓም እንደሌለውእንዳልኾን ምከሩኝ፤ አልፎ ተርፎም በማትስማሙበት አስተሳሰቦቼ አንጻር ሞግቱኝ፡፡ ብረት ብረትን እንዲስል እንዲሁ ባልንጀራም ባልንጀራውን እንደሚስለው ንጉሥ ሰሎሞን ተናግሯል አይደል! በተቀረው፣ በጸሎታቸሁ እንድሰጥ ልባዊ ልመናዬ ነው፡፡ በዚህ ተግባር ከጸጋው ድጋፍ በቀር ሩቅ መጓዝ እንደ እልም ነውና፡፡ የሚያሳድግ አምላክ ይርዳኝ እንጂነበርተብሎ መዘከርስ አለ አይደለም ወይ?
ወደ እግዚአብሔር አምላካችንም እንዲህ እላለሁ፣አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘላለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ። እንዲህ ብለሃልና፡- ምሕረት ለዘላለም ይመሠረታል፥ እውነትህም በሰማይ ይጸናል” (መዝ ፹፱÷-)፡፡ እውነተኛው አምላክ (ዮሐ ፲፯÷) ለእውነት መኖርን ያብዛልን፡፡ መልካም ዐዲስ ዓመት!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
እንን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገረዎ!